የአብዛኞቹ ዩንቨርስቲዎች የውጤት አሰራር /Grading System/ ተመሳሳይ ነው። በእያንዳንዱ ወሰነ-ትምህርት / ሴሚስተር/፡ ከ20 ወይም ከ30%(ፈተናዎች፣የቡድን እና የግል አሳይመንቶች) ሊይዙ ይችላሉ። ከ20 ወይም ከ30% (የአጋማሽ ፈተናዎች Mid Exam)፣ ከ50% ደግሞ የማጠቃለያ ፈተናዎች(Final Exam) ድርሻቸውን ይይዛሉ። ለእያንዳንዱ የምትወስዱት ኮርስ የሶስቱ ድምር ውጤት ሴሚስተር መጨረሻ ላይ በመደመር ለጠቅላላ ኮርሶቹ ተካፍሎ ውጤት/ግሬድ/ ይሰራላችኋል።
GPA ማለት በሁሉም ሴሚስተር የምታስመዘግቡት ውጤት ሲሆን CGPA ማለት አማካይ ውጤት /Grade/ ማለት ነው። በመጀመሪያው ሴሚስተር የተጠቀሱትን አምስት የትምህርት መስኮች መቀላቀል የምትፈልጉ ተማሪዎች ለውድድር የሚታየው የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት (first semester ) GPA ብቻ ይሆናል ፤ የተቀሩትን የትምህርት መስኮች መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ግን የሁለቱም ሴሚስተር Average or CGPA የሚያዝ ይሆናል ማለት ነው።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር 20% entrance , 30% PRE-FEILD(COC) በሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ላይ ተግባራዊ የሚያደርግ ይሆናል። የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤት /ግሬድ/ 50%ግን ማንኛውንም የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትልቁን ድርሻ ይይዝላቹኋል።
ስለሆነም 20%ቷ እውን ከሆነች የማትሪክ ውጤት (entrance exam) ስለተበላሸብኝ ብላቹህ ተስፋ አትቁረጡ ።
የዩንቨርስቲ ውጤት አሰራርን በምሳሌ እንየው።
የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት እነዚህ ናቸው ብንልና የኮርሶቹም ECTS እንደሚከተለው ቢሆን
Critical thinking #5Ects
Psychology #5Ects
General Physics #5Ects
English #5Ects
Geography #5Ects
Mathematics #5Ects
Physical fitness (pass or fail)
Total credit hours #31Ects
አንድ ተማሪ በመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት/ ሴሚስተር ያስመዘገበው ውጤት ይሄንን ይመስላል እንበል።
1) Critical thinking—> 77 B+
2) Psychology—>82 A-
3) Gen’ Physics—>59.5 C
4) Mathematics—>42 D
5) English—>68 B
6) Geography—>64 C+
እነዚህን ውጤቶች በቅደም ተከተል calculate ለማድረግ እና የተማሪውን ውጤት ለማወቅ ምን እናድርግ!?
Credit hour × grade
5×3.5 =17.5
5×3.75 =18.75
5×2 =8
5×1 =5
5×2.75 =13.75
5×2.5 = 12.5
Total sum=75.5
Semister grade =Total sum÷Total credit hour
76.5÷30=2.5166 GPA
ስለዚህ ይህ ተማሪ በመጀመሪያው ሴሚስተር የሰራው ግሬድ 2.52 ይሆናል ማለት ነው።
የአንደኛ አመት ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር የሚያስመዘግቡት ውጤት /ግሬድ/ እንደሚከተለው ወደ ቀጣዩ ሴሚስተር የማሳለፍ እና ያለማሳለፍ ደረጃ ይኖራቸዋል።
GPA
1.75-4.00
( ተማሪው ሙሉ በሙሉ ያሳልፋል )
1.50-1.75
( ተማሪው በማስጠንቀቂያ ማለፍ ይችላል )
1.00-1.50
( ተማሪው ለአንድ አመት ያክል ከትምህርት ይታገዳል )
0.00-1.00
(*ተማሪው ሙሉ ለሙሉ ከትምህርት አለም ይታገዳል )
ከዚህ ውጭ ደግሞ በአንድ ሴሚስተር ሶስት ኮርሶችን F የውጤት ደረጃ ያመጣ ተማሪ አንድ ሴሚስተር እንዲዘገይ (Lag) ይደረጋል።
ኤድማፕ፣ መሰል ለአዳዲስ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች መረጃዊዎችን መስጠቱን ይቀጥላል።